Hepatitis B Foundation President Dr. Chari Cohen is quoted in a powerful new story about hepatitis B in The New Yorker. You can read it here.

አጠቃላይ መረጃ  

ሄፓታይተስ ቢ ምንድን ነው?

ሄፓታይተስ ቢ በዓለም ላይ በብዛት ጉበትን ከጥቅም ውጭ የሚያደርግ ነው፡፡ የሚመጣውም ሄፓታይተስ ቢ (HBV) በሚባል ቫይረስ ሲሆን ቫይረሱ ጉበትን በማጥቃት ጉዳት ያደርሳል፡፡ የሚተላለፈው በደም፣ ጥንቃቄ በጎደለው የግብረ ስጋ ግንኙነት፣ መርፌዎችን በመጋራት ወይም ድጋሚ በመጠቀም እንዲሁም በበሽታው ከተያዘች እናት ወደ ልጅ በእርግዝና ወይም በወሊድ ወቅት ነው፡፡ በርካታ በበሽታው የተያዙ ጎልማሶች ሄፓታይተስ ቢ ን ያለምንም ችግር ከሰውነታቸው እንዲወገድ ማድረግ ችለዋል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ጎልማሶች እና በበሽታው በጣም የተጠቁ ህፃናት እና ታዳጊዎች ቫይረሱን ከሰውነታቸው ማስወጣት አለመቻላቸውን ተከትሎ በፀና ህመም ውስጥ ገብተዋል፡፡

መልካሙ ዜና ሄፓታይተስ ቢ ን ለመከላከል አስተማማኝ ክትባት መኖሩ ሲሆን፤ ሌላው ደግሞ ቀድሞውኑ በሄፓታይተስ ቢ ለተጠቁት በአዲስ መልኩ ህክምና መደረጉ ነው፡፡ 

በሄፓታይተስ ቢ የተጠቁት ሰዎች ምን ያህል ናቸው?

በመላው ዓለም 2 ቢሊየን ሰዎች (ከ3 ሰዎች መካከል1) በሄፓታይተስ ቢ የተጠቁ ሲሆን 257 ሚሊየን የሚሆኑት ሰዎች ደግሞ በፀና የታመሙ ናቸው፡፡ (ይህም ማለት ቫይረሱን ከሰውነታቸው ማስወገድ አይቻልም) በሄፓታይተስና ከእሱ ጋር በተያያዘ 700,000 የሚጠጉ ሰዎች በየዓመቱ ለህልፈት ይዳረጋሉ፡፡

ሄፓታይተስ ቢ በአንዳንድ የዓለም ክፍሎች ለምን በብዛት ይከሰታል?

ሄፓታይተስ ቢ የእድሜ እና የብሄር ልዩነት ሳያደርግ ሁሉንም ሰው ሊይዝ ይችላል፤ ነገር ግን ሄፓታይተስ ቢ በብዛት በሚከሰትባቸው ከተወሰኑ የዓለም ክፍሎች ያሉ ሰዎች ማለትም እንደ ኤሲያ፣ የአፍሪካ የተወሰኑ ክፍሎች፣ ደቡብ አሜሪካ፣ ምዕራብ አውሮፓ እና መካከለኛው ምስራቅ በበሽታው የመያዝ እድላቸው በእጅጉ ከፍ ያለ ነው፡፡ በነዚህ ቦታዎች በተወለዱ አሜሪካውያን (ወይም ቤተሰቦቻቸው በተወለዱት) ላይ ሄፓታይተስ ቢ በብዛት ይከሰታል፡፡

ሄፓታይተስ ቢ በተወሰኑ የኣለማችን ክፍሎች ላይ በብዛት የተለመደ ሲሆን፤ ለዚህ ደግሞ በምክንያትነት የሚጠቀሰው በቦታዎቹ ላይ ቀደም ብለው በሄፓታይተስ ቢ የተጠቁ ብዙ ሰዎች መኖራቸው ነው፡፡ ምንም እንኳን ሄፓታይተስ ቢ "የኤስያውን በሽታ" ወይም "የአፍሪካውያን በሽታ" ባይሆንም ከነዚህ ቦታዎች በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የበከለ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎም በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎችም የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስን ወደሌሎች እንዲተላለፍ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ስጋቱ በጨመረ ቁጥር በቫይረሱ ሊያዙ ይችላሉ፡፡ በቫይረሱ የተያዙ ምዕራባውያን ቁጥር ማነሱን ተከትሎ፣ ይህ ቡድንያለው የመያዝ እድሉ ዝቅ ያለ ነው፡፡

ሄፓታይተስ ቢ በብዛት በሚታይባቸው አካባቢዎች ያሉ ሰዎች በብዛት የሚያዙት በወሊድ ጊዜ ማለትም እናቶች ሲወልዱ ባለማወቅ ቫይረሱ ወደ ልጃቸው ይተላለፋል፡፡ ታዳጊ ህፃናት የሚኖሩት ቫይረሱ ካለበት የቤተሰቡ አባል ጋር በየቀኑ የቀረበ ግንኙነት የሚደርጉ ከሆነ የመያዝ እድል አላቸው፡፡ ህፃናትና ታዳጊዎች በሄፓታይተስ ቢ ከሌሎች በበለጠ በከፍተኛ ደረጃ ይጠቃሉ፤ ለዚህም ምክንያቱ ብዙም ያልጠነከረው በሽታን የመከላከል አቅማቸው ቫይረሱን ለማስወገድ ስለሚቸገር ነው፡፡

እርስዎ አሊያም የእርስዎ ቤተሰብ በካርታው ላይ በጥቁር ሰማያዊ የመጡ ከሆነ በሄፓታይተስ ቢ የመያዝ እድልዎ በእጅጉ ከፍ ያለ ስለሚሆን ምርመራ ለማድረግ ዶክተሮችን ማናገር አለብዎ፡፡

map 3 04 global 002

 

ስለ ሄፓታይተስ ቢ ለምንድን ነው ትኩረት መስጠት ያለብኝ?

ስር የሰደደ ሄፓታይተስ ቢ የከፋ የጉበት ህመምን ማለትም እንደ ሰርሆሲስ ወይም የጉበት ካንሰርን ያስከትላል፡፡ ምርመራ ማድረግ ጠቃሚ ነው፤ ምክንያቱም ቀድሞ ምርመራ ማድረግ ቀድሞ ህክምና ለማግኘትና የግለሰቡንም ህይወት ለማዳን ያግዛል፡፡ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቫይረሱን ወደ ሌሎች ያስተላልፋሉ፡፡ በርካቶች አለመያዛቸውን ባለማወቃቸው የተነሳ፣ ሳያውቁ ቫይረሱን ወደ ብዙ ሰዎች ያስተላልፋሉ፡፡ ሰዎች ምርመራ ካላደረጉ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ሄፓታይተስ ቢ ወደ ተለያየ ትውልድ ብሎም ማህበረሰብ የሚተላለፍ ነው፡፡

በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ትውልዶች መያዛቸውን ተከትሎ ሄፓታይተስ ቢ "በመወለድ የሚመጣ ነው" የሚል አንድ የተለመደ አባባል አለ፡፡ ነገር ግን ሄፓታይተስ ቢ በዘር የሚመጣ በሽታ አይደለም፣ ሄፓታይተስ ቢ የሚመጣው በቫይረስ፣ እንዲሁም በብዛት በቤተሰብ አባላት መካከል ከእናት ወደ ልጅ ወይም በድንገተኛ አጋጣሚ በተፈጠረ የደም ንክኪ ነው፡፡ ቤተሰቦች በሄፓታይተስ ቢ የመያያ ኡደትን በመመርመር፣ ክትባት በመከተብ እና ህክምና በመከታተል ማስቆም ይችላሉ፡፡

ሄፓታይተስ ቢ ለምንድን ነው እጅግ አደገኛ የሆነው?

ሄፓታይተስ ቢ አደገኛ ነው፤ ምክንያቱም "ዝምተኛው በካይ" በመሆኑ ሰዎች ምንም ነገር ሳያውቁ ስለሚይዛቸው ነው፡፡  በሄፓታተስ ቢ የተያዙ በርካታ ሰዎች ስለመያዛቸው አለማወቃቸውን ተከትሎ ቫይረሱንበደማቸው እና በሌሎች በተበከሉ የሰውነታቸው ፈሳሾች ወደ ሌሎች ያዛምታሉ፡፡ በፀና የታመሙት ጉበታቸው ስራ የማቆም ስጋት እንዲሁም በስተመጨረሻም ሲርሆሲስ ወይም የጉበት ካንሰር የመከሰታቸው እድል ይጨምራል፡፡ ቫይረሱ ለብዙ ዓመታት ድምፁን አጥፍቶ ሳይለይ ከቆየ በጊዜ ሂደት በተከታታይ ዓመታት በጉበት ላይ ጉዳት ያደርሳል፡፡ 

በመጀመሪያ ደረጃ ያለ ሄፓታይተስ ቢ ምንድን ነው?

የበመጀመሪያ ደረጃ ላይ ያለ ሄፓታይተስ ቢ እስከ ስድስት ወር (በምልክት ወይም ያለ ምልክት) ድረስ ያለውን ጊዜ የሚመለከት ሲሆን በዚሁ ጊዜም የተያዘው ግለሰብ ቫይረሱን ወደ ሌሎች ማስተላለፍ ይችላል፡፡

በጅማሮ ደረጃ ላይ ያለ ሄፓታይተስ ቢ ምልክቶች የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ የመገጣጠሚያ እና ጡንቻ ህመም፣ ዝቅተኛ መጠን ያለው ትኩሳት እና የጨጓራ ህመምም ሊኖር ይችላል፡፡ ምንም እንኳን በርካታ ሰዎች ላይ ምልክቱ ባይታይም፣ በቫይረሱ ከተያዙ ከ60-150 ቀናት በኋላ ቫይረሱ ሊገኝባቸው የሚችል ሲሆን፤ ይህም በአማካይ 3 ወር ማለት ነው፡፡ አንዳንድ ሰዎች ጠንከር ያሉ ምልክቶች የሚታይባቸው ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ንፍጥ፣ ማስመለስ፣ ጃውንዳይስ (የዓይን እና ቆዳ ቢጫ መሆን) አሊያም የጨጓራ መነፋት ሲሆኑ፣ ወደ ጤና ባለሙያ እንዲሄዱ ምክንያት ይሆናል፡፡

ቀላል የሚባል የደም ምርመራ ለአንድ ግለሰብ በደም ውስጥ የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ስለመኖሩ ሊነግረው ይችላል፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ላለ ሄፓታይተስ ቢ ምርመራ አድርገው ከሆነ ከ6 ወራት በኋላ ዶክተሩ በድጋሚ ደሞትን በመመርመር እንደተሻለዎት አሊያም ሄፓታይተስ ቢ እንደፀናብዎት ማረጋገጥ አለበት፡፡ የጤና ድጋፍ ባለሙያው በደሞት ውስጥ የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ አለመኖሩን እስኪያረጋግጥልዎት ድረስ ወደሌሎች ላለማስተላለፍ ጥረት ማድረግ አለብዎት፡፡ የወሲብ አጋርዎ (አጋርዎችዎ) እና የቤተሰብ አባላት (በአንድ ቤት ውስጥ በጋራ የምትኖሩ) የሄፓታይተስ ቢ ምርመራ ማድረግ አለባቸው፡፡ ምናልባትም በቫይረሱ ያልተያዙ ከሆኑ እና የሄፓታይተስ ቢ ን ክትባት ያልወሰዱ ከሆኑ ክትባቱን በተከታታይ መውሰድ አለባቸው፡፡   

በመጀመሪያ ደረጃ ሄፓታይተስ ቢ ላለባቸው ሰዎች የሚሰጥ የሄፓታይተስ ቢ ህክምና የለም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ያለውን ሄፓታይተስ ቢ ለማስወገድ የሚደረግ ህክምና ስለሌለ የተያዙ ጎልማሶች በራሳቸው ጊዜ ይሻላቸዋል፡፡ አንዳንዴ ምልክቶቹ በፀና የሚታይበት ህመምተኛ ለአጠቃላይ ድጋፍ ሲባል ህክምና ሊደረግለት ይችላል፡፡ እረፍት እንዲያገኙ ማድረግ እና ምልክቶቹን መቆጣጠር የዚህ ህክምና ቀዳሚ ግቦች ናቸው፡፡ አልፎ አልፎ የሚከሰት፣ ህይወትን አደጋ ውስጥ የሚከተው “ፉልሚናንት ሄፓታይተስ”በመጀመሪያ ደረጃ የቫይረሱ መያዝ ወቅት ሊከሰት የሚችል ሲሆን፤ ይህም ግለሰቡን ለድንገተኛ የጉበት ስራ ማቆም ሊዳርገው ስለሚችል ወዲያውኑ በፍጥነት ፈጣን የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ መደረግ አለበት፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ ላለ የሄፓታይተስ ቢ ምልክቶች ጠቃሚ ከሆኑት ምክሮች መካከል አልኮልን አለመጠቀም፣ ሲጋራን አለማጨስ ወይም መቀነስ፣ ጤናማ አመጋገብን መከተል፣ ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች አለመመገብ፣ ከጤና ባለሙያ ጋር በሚወስዷቸው ማናቸውም መድሀኒቶች ዙሪያ መመካከር (በትዕዛዞች፣ በመድሀኒት አወሳሰድ፣ በሚወስዷቸው ቫይታሚኖችና ሌሎች የባህል መድሀኒቶች ዙሪያ)፡፡ ይህ ያሏችሁን ማናቸውንም ሌሎች ጥያቄዎች ለመጠየቅ ጥሩ ጊዜ ነው፡፡ ቫይታሚኖችን እና በምግብ መልክ የሚወሰዱ መድሀኒቶች መጠቀም እንዳይድኑ ከማድረግ ይልቅ በጉበት ላይ የበለጠ ጉዳት እንዲደርስ ያደርጋሉ፡፡  

በመጀመሪያ ደረጃ ላይ ካለ የቫይረሱ መያዝ ለመዳን በህክምና ባለሙያ የሚደረግልዎትን ማንኛውንም አይነት የደም ምርመራ በአግባቡ መከታተል አለብዎት፡፡

 

ስር የሰደደ ሄፓታይተስ ቢ ምንድን ነው?

ከስድስት ወር በኋላ (ከመጀመሪያው የደም ምርመራ ውጤት በኋላ) የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ እንዳለባቸው ያወቁ ሰዎች በሽታው ስር ስለመስደዱ ለማረጋገጥ ምርመራ ማድረግ አለባቸው፡፡ ይህም ማለት የሰውነታቸው በሽታን የመከላከል አቅም የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስን ለማስወገድ ባለመቻሉ በሰውነታቸው በደምና በጉበት ውስጥ እንዲቆይ ይሆናል፡፡ ስር የሰደደን ህመም ለማከምና ለማገዝ የሚደረግ ውጤታማ አሰራር ቢኖርም በሽታውን ግን ማዳን አይቻልም፡፡ በሽታው ስር ከሰደደ በቀሪው የህይወት ዘመንዎ ከቫይረሱ ጋር አብረው ይኖራሉ፡፡

ስር የሰደደ የሄፓታይተስ ቢ ያለባቸው ሰዎች ባለማወቅ ቫይረሱን ወደ ሌሎች ሰዎች ያስተላልፋሉ፡፡ ስር የሰደደ የሄፓታይተስ ቢ ወደ ጠነከረ የጉበት ህመም ማለትም ወደ ሰርሆሲስ ወይም የጉበት ካንሰር ያመራል፡፡ በፀና የታመመ ሰው ሁሉ የጠነከረ የጉበት ህመም ይይዘዋል ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን በበሽታው ምንም ካልተያዘው ሰው በበለጠ የመያዝ እድል አለው፡፡

ስር የሰደደ ሄፓታይተስ ቢ የመፈጠር እድሉ ግለሰቡ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቫይረሱ በተጋለጠበት እድሜ ይወሰናል፡፡

  • 90% በሚሆኑትና በቫይረሱ በሚያዙት አዲስ የተወለዱ ጨቅላ ህፃናት እና ልጆች ላይ ሄፓታይተስ ቢ ስር ይሰዳል፡፡
  • እስከ 50% የሚደርሱትና በቫይረሱ የተያዙ ህፃናት (ከ1-5 ዓመት) ስር ለሰደደ የሄፓታይተስ ቢ ይዳረጋሉ፡፡
  • 5-10% የሚሆኑት በቫይረሱ የተያዙ ጎልማሶች ስር ለሰደደ የሄፓታይተስ ቢ ይጋለጣሉ (ከነዛ ውስጥ 90% ያገግማሉ)

ስር የሰደደ የሄፓታይተስ ቢ እንዳለ ማወቅ በእጅጉ የሚረብሽ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም አብዛኞቹ ሰዎች ምልክቶቹ ባለመታየታቸው ለሄፓታይተስ ቢ ምርመራ የሚያደርጉት በቫይረሱ ከተያዙ ከአስርት አመታት በኋላ በመሆኑ ስር ለሰደደው የሄፓታይተስ ቢ ምርመራ ማድረግ የሚያስደነግጥና የሚያስገርም ሊሆን ይችላል፡፡ መልካም የሚባለው ዜና አብዛኞቹ ስር ከሰደደ የሄፓታይተስ ቢ ጋር ያሉ ሰዎች ረዥምና ጤናማ ኑሮ እንደሚኖሩ መጠበቅ አለባቸው፡፡

በቫይረሱ የተያዘች ነፍሰ ጡር እናት በወሊድ ወቅት አዲስ ወደተወለደው ልጅዋ ቫይረሱን ልታስተላልፍ ትችላለች፡፡ ስለሆነም አዲስ የሚወለዱት ጨቅላ ህጻናት በወሊድ ወቅት የመያዝ እድላቸው ከፍ ስለሚልና ከተያዙም ስር ስለሚሰድባቸው፣ ዓለም አቀፉ ጤና ድርጅት እና በአሜሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል ሁለቱም ሁሉም ህፃናት እንደተወለዱ በ 12-24 ሰአታት ውስጥ የሄፓታይተስ ቢ ክትባትን መውሰድ እንዳለባቸው በጋራ ይመክራሉ፡፡ ነፍሰ ጡር ከሆኑ እና በቫይረሱ መያዝዎትን ካወቁ የወለዱት ልጅዎ በተወለደ ከ12-24 ባሉት ሰዓታት የሄፓታይተስ ቢ ክትባት ማግኘት አለበት፡፡

የሄፓታይተስ ቢ በሽታን ማዳን ባይቻልም የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስን የሚቆጣጠርና በጉበት ላይ ጉዳት እንዳያመጣ የሚስቆም ውጤታማ መድሀኒት አለ፡፡ በጥናት ላይ ያለና ወደፊት በሽታውን ማዳን እንደሚችል ተስፋ የተጣለበት አዲስ መድሀኒት ወደፊት ይመጣል፡፡ ምንም እንኳን ከባድ የጉበት ህመም ወይም የጉበት ካንሰር የመከሰቱ እድል በቫይረሱ ካልተያዙት በበለጠ ስር በሰደደ የሄፓታይተስ ቢ ህሙማን ላይ ቢታይም፤ ግለሰቡ ሊተገብራቸው የሚገቡና ችግሩን ለመቀነስ የሚረዱ ቀላል ተግባራት አሉ፡፡

  • በየስድስት ወሩ (አለበለዚያም በዓመት አንድ ግዜ) የጉበት ስፔሻሊስት ወይም ስለ ሄፓታይተስ ቢ እውቀቱ ወዳለው የጤና ባለሙያ በመሄድ የጉበትዎን ጤንነት ማስመርምር ያስፈልጋል፡፡
  • ከጤና ባለሙያዎ ጋር ስር ለሰደደው የሄፓታይተስ ቢ የሚደረግልዎት የህክምና ክትትል የከፋ የጉበት ህመም ወይም የጉበት ካንሰር እንዳይከሰት ለመከላከል እንደሚረዳ ተነጋገሩ፡፡
  • ወደ ጤና ተቋም በሚሄዱበት ጊዜ የጤና ባለሙያው ለጉበት ካንሰር እርስዎን መምረጡን እርግጠኛ መሆንዎ፤ ቫይረሱን ቀድሞ በመለየት የበለጠ ህክምና እንዲያገኙና ህይወትዎ እንዲረዝም ለማድረግ ስለሚረዳ ነው፡፡
  • በጉበትዎ ላይ በርከት ያሉ መጨናነቆችን ስለሚያስከትሉ አልኮል እና ማጨስን ያስወግዱ አሊያም ይቀንሱ፡፡
  • ቅባት የበዛባቸው ምግቦች ለጉበት ስለሚከብዱ፣ የበሰሉ አትክልቶችን በመመገብ ጤናማ አመጋገብይኑረን፡፡

 

“በሽታው ስር የሰደደበት” ማለት ምን ማለት ነው?

የሆነ አንድ ግለሰብ በሄፓታይተስ ቢ በፅኑ ከታመመ፣ ዶክተሩ “በፅኑ የታመመ”ብሎ ወደ ሌሎች ይልከዋል፡፡ “በፅኑ የታመመ”ማለት ግለሰቡ ስር ሰደደ ሄፓታይተስ ቢ ያለበት እና ቫይረሱን ወደሌሎች ማስተላለፍ የሚችል እንደሆነ እንዲሁም በዶክተር ክትትል ሊደረግለት እንደሚገባ ለማመላከት ነው፡፡

 

ለሄፓታይተስ ቢ ህክምና አለው?

አንዳንድ ጎልማሶች ያለምንም መድሀኒት በመጀመሪያ ደረጃ ካለ የቫይረሱ መያዝ ራሳቸውን ያድናሉ፡፡ ስር በሰደደ ሄፓታይተስ ቢ ለተያዙ ጎልማሶች፣ ህፃናት እና ጨቅላ ህፃናት ምንም አይነት መድሀኒት የለም፡፡ ነገር ግን መልካም የሚባለው ዜና በፀና በታመመው ህመምተኛ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቫይረሱን በማዳከም የከፋ ደረጃ ላይ ሊደርስ የሚችለውን የጉበት ህመም መቀነስ የሚያስችል ህክምና አለ፡፡ የሚራቡት የሄፓታይተስ ቢ ቫይረሶች ቁጥር በቀነሰ ጊዜ በጉበት ላይ የሚደርሰው ጉዳትም ይቀንሳል፡፡

ያሉት ተስፋ ሰጪ ምርምሮች ሲታዩ፣ ወደፊት ስር የሰደደውን ሄፓታይተስ ቢ ለማከም የመረዱ መድሀኒቶች እንደሚገኙ ታላቅ ተስፋ አለ፡፡ የእኛንይጎብኙ መድሀኒት ተመልከት በመሞከር ላይ ያሉ የመድሀኒት ዝርዝሮችን ለማየት፡፡

የእኔን ሄፓታይተስ ቢ ን ለማከም ምን አማራጮች አሉ?

በመጀመሪያ ደረጃ ላለ የቫይረሱ መያዝ እረፍት ከማድረግና ማንኛውንም የበሽታውን ምልክቶች ከመቆጣጠር የዘለለ ምንም አይነት ህክምና የለም፡፡ 

ስር ለሰደደ ሄፓታይተስ ቢ የተለያዩ ህክምናዎች አሉ፡፡ በሄፓታይተስ ቢ በፅኑ የታመመ ሰው ሁሉ ህክምና እንደማያስፈልገው መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ህክምና እንደሚስፈልግህ አሊያም ሁኔታውን አየተከታተልክ ለመጠበቅ እንድትወስን ዶክተርህ ያግዝሀል፡፡

የተለያዩ የአንቲቫይራል ህክምናዎች የሄፓታይተስ ቢ ን ቫይረስ ከመባዛት ይገታሉ አሊያም ይቀንሳሉ፤ ይህም በጉበት ላይ የሚደርሰውን የማቃጠል ስሜት እና መሰል ጉዳትን ለመቀነስ ይረዳል፡፡ እነዚህ አንቲቫይራሎች በፒል መልክ በቀን አንድ ጊዜ ቢያንስ ለ 1 ዓመትና ከዚያም በላይ በፒል መልክ ይወሰዳሉ፡፡ በአሜሪካ 6 በኤፍ.ዲ.ኤ እውቅና የተሰጣቸው አንቲቫይራሎች አሉ፤ ነገር ግን ሶስቱ “በመጀመሪያው መስመር ያሉ”የሚባሉት አንቲቫይራሎች ይመከራሉ፦ቴኒፎቪር ዲሶፕሮክሲል (ቪሬድ/ቲ.ዲ.ኤፍ)፣ ቴኖፎቪር አላፍናማይድ (ቬምሊዲ/ቲ.ኤ.ኤፍ) እና ኢንትካቪር (ባራክሉድ)፡፡ መጀመሪያው መስመር ላይ ያሉት አንቲቫይራሎች አስተማማኝና በጣም ውጤታማ በመሆናቸው ይመከራሉ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ያሉት የሚባሉት አንቲቫይራል ህክምናዎች ውጤት ካላመጡ ወይም አንሱን የማግነት እድል ከሌላቸው ሌሎች አማራጮች አሉ፦ telbuvidine (Tyzeka፣ Sebivo)፣ adefovir dipivoxil (Hepsera)፣ እና lamivudine (Epivir-HBV፣ Zeffix፣ Heptodin)፡፡

ምንም እንኳን ኤፍ.ዲ.ኤ እነዚህን አንቲቫይራሎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ቢመክርም ስር የሰደደውን ሄፓታይተስ ቢ ን ሙሉ በሙሉ ማከም አይችሉም፡፡ ነገር ግን በጉበት ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት እና የጉበት ካንሰርን ለመቀነስ ይችላሉ፡፡ አንቲቫይራሎች ዝም ተብለው የሚወሰዱ እና የሚቆሙ ባለመሆናቸው ለሄፓታይተስ ቢ ተብሎ የሚደረገውን ህክምና ከመጀመር በፊት እውቀቱ ያለው ዶክተር ጥልቅ ምርመራ ማድረግ አለበት፡፡

ኢሚዩኖሞዱሌተር መድሀኒቶች የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስን በመቆጣጠር የሰውነት የመከላል ብቃትን ከፍ ያደርጋል፡፡ ከ 6 ወር እስከ 1 ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ በመርፌ የሚሰጡ ናቸው፡፡ በብዛት የታዘዘው ኢንተርፌሮን አልፋ-2b (Intron A) እናፔጊሌትድ ኢንተርፌሮን (Pegasys) ናቸው፡፡

እርስዎና ዶክተርዎ ካሉት የህክምና አማራጮች መካከል ለእርስዎ የተሻለውን ለመምረጥ እንዲቻል መነጋገር አለባችሁ፡፡ ለአብዛኞቹሰዎች መድሀኒቶቹ የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስን ወይ ይቀንሳሉ አሊያም ያስቆማሉ፡፡ በጥቂት ወራት ውስጥ ህመምተኛው የተሻለ ስሜት ይሰማዋል፤ ምክንያቱም ጉበቱ ላይ በቫይረሱ እየደረሰበት የነበረው ጉዳት እየቀነሰ ይመጣል፤ አሊያም ለረዥም ጊዜ ሲወሰድ ድጋሚ ሊያገረሽም ይችላል፡፡

በኤፍ.ዲ.ኤ ለተረጋገጠ የተሟላ የመድሀኒት ዝርዝር እና በሄፓታይተስ ቢ ዙሪያ እየተሰሩ ላሉ ተስፋ ሰጪ መድሀኒቶች፣ ይጎብኙ መድሀኒት ተመልከት፡፡

 

 

General Information

What is hepatitis B?
Hepatitis B is the world's most common liver infection. It is caused by the hepatitis B virus (HBV), which attacks and injures the liver. It is transmitted through blood, unprotected sex, shared or re-used needles, and from an infected mother to her newborn baby during pregnancy or delivery. Most infected adults are able to get rid of the hepatitis B virus without any problems. However, some adults and most infected babies and children are unable to get rid of the virus and will develop chronic (life-long) infection.

The good news is that there is a safe vaccine to prevent a hepatitis B infection and new treatments for those already infected with hepatitis B.


How many people are affected by hepatitis B?
Worldwide, 2 billion people (1 out of 3 people) have been infected with hepatitis B; and 257 million people are chronically infected (which means they are unable to get rid of the virus). An estimated 700,000 people die each year from hepatitis B and its complications.


Why is hepatitis B more common in some parts of the world?
Hepatitis B can infect any person of any age or ethnicity, but people from parts of the world where hepatitis B is common, such as Asia, parts of Africa and South America, Eastern Europe, and the Middle East, are at much higher risk for getting infected. Hepatitis B is also common among Americans who were born (or whose parents were born) in these regions.

Hepatitis B is more common in certain regions of the world because there are so many more people already infected with hepatitis B in these regions. Although hepatitis B is not an "Asian disease" or an “African disease,” it affects hundreds of millions of people from these regions – so there are more people who can pass the hepatitis B virus on to others. This increases the risk that you could get infected. Since there is a smaller number of Westerners who are infected, this group has a lower risk of infection.

In regions where hepatitis B is common, people are usually infected as newborns - from a mother who unknowingly passes the virus to her baby during delivery. Young children are also at risk if they live in close daily contact with an infected family member. Babies and children are more likely to develop a chronic hepatitis B infection because their young immune systems have trouble getting rid of the virus.

If you, or your family, is from an area of the map that is darker blue, you might be at greater risk for hepatitis B infection and should talk to a doctor about getting tested.

map 3 04 global 002


Why should I be concerned about hepatitis B?
Chronic hepatitis B can lead to serious liver disease such as cirrhosis or liver cancer. It's important to get tested because early diagnosis can lead to early treatment which can save your life. Also, people who are infected can spread the virus to others. Since most people don't know they are infected, they are unknowingly spreading it to many other people. If people are not tested, hepatitis B can pass through several generations in one family and throughout the community.

One common myth is that hepatitis B can be "inherited" since several generations in one family may be infected. But hepatitis B is NOT a genetic disease -- hepatitis B is caused by a virus, which is often transmitted among family members due to mother-to-child transmission or accidental household exposure to blood. Families can break the cycle of hepatitis B infection by getting tested, vaccinated and treated.


Why is hepatitis B so dangerous?
Hepatitis B is dangerous because it is a “silent infection” that can infect people without them knowing it. Most people who are infected with hepatitis B are unaware of their infection and can unknowingly pass the virus to others through their blood and infected bodily fluids. For those who become chronically infected, there is an increased risk of developing liver failure, cirrhosis and/or liver cancer later in life. The virus can quietly and continuously attack the liver over many years without being detected.


What is acute hepatitis B?
An acute hepatitis B infection may last up to six months (with or without symptoms) and infected persons are able to pass the virus to others during this time.

Symptoms of an acute infection may include loss of appetite, joint and muscle pain, low-grade fever, and possible stomach pain. Although most people do not experience symptoms, they can appear 60-150 days after infection, with the average being 3 months. Some people may experience more severe symptoms such as nausea, vomiting, jaundice (yellowing of the eyes and skin), or a bloated stomach that may cause them to see a health care provider.

A simple blood test can tell a person if the hepatitis B virus is in their blood. If you have been diagnosed with acute hepatitis B, the doctor will need to test your blood again in 6 months to figure out if you have recovered, or if you have developed a chronic hepatitis B infection. Until your health care provider confirms that your blood test shows that there is no more hepatitis B virus in your blood, it is important to protect others from a possible infection. It is also important to have your sexual partner(s) and family members (or those you live in close household contact with) tested for hepatitis B. If they have not been infected – and have not received the hepatitis B vaccine – then they should start the hepatitis B vaccine series.

People who have acute hepatitis B are not prescribed specific hepatitis B treatment – there is no treatment that will get rid of an acute hepatitis B infection, and most people infected as adults recover on their own. Sometimes, a person with severe symptoms may be hospitalized for general support. Rest and managing symptoms are the primary goals of this medical care. A rare, life-threatening condition called “fulminant hepatitis” can occur with a new acute infection and requires immediate, urgent medical attention since a person can go into sudden liver failure.

Simple tips for taking care of your liver during an acute hepatitis B infection are to avoid alcohol, stop or limit smoking, eat healthy foods, avoid greasy or fatty foods, and talk to your health care provider about any medications you are taking (prescriptions, over-the-counter medications, vitamins or herbal supplements) to make sure they are safe for your liver. This is a good time to ask any other questions you may have. The use of vitamins and liver health supplements will likely not assist your recovery and may actually cause more harm than good to the liver.

Be sure to follow-up with your health care provider for any additional blood tests that are needed to confirm your recovery from an acute infection.

What is chronic hepatitis B?
People who test positive for the hepatitis B virus for more than six months (after their first blood test result) are diagnosed as having a chronic infection. This means their immune system was not able to get rid of the hepatitis B virus and it still remains in their blood and liver. There are effective ways to treat and manage a chronic infection, but there is no cure. If you are chronically infected, the virus will likely remain in your blood for the rest of your life.

People who have chronic hepatitis B can unknowingly pass the virus on to others. Chronic hepatitis B can also lead to serious liver diseases, such as cirrhosis or liver cancer. Not every person who is chronically infected will develop serious liver disease. However, they have a greater chance than someone who is not infected.

The risk of developing a chronic hepatitis B infection is related to the age at which one first becomes infected with the hepatitis B virus:

  • 90% of infected newborns and babies will develop a chronic hepatitis B infection
  • Up to 50% of infected children (1-5 years) will develop a chronic hepatitis B infection
  • 5-10% of infected adults will develop a chronic hepatitis B infection (that is, 90% will recover)

Learning that you have a chronic hepatitis B infection can be very upsetting. Because most people do not have symptoms and can be diagnosed decades after their initial exposure to the hepatitis B virus, it can be a shock and a surprise to be diagnosed with a chronic hepatitis B infection. The good news is that most people with chronic hepatitis B should expect to live a long and healthy life.

Infected pregnant women can pass the virus to their newborns during childbirth. Therefore, since the risk of newborns becoming chronically infected at birth is high, both the World Health Organization (WHO) and the U.S. Centers for Disease Control and Prevention (CDC) recommend that all infants receive the first dose of the hepatitis B vaccine within 12-24 hours after birth. If you are pregnant and you know that you are infected, you can make sure that your baby gets the first dose of the hepatitis B vaccine within 12-24 hours after delivery!

While there is no cure for chronic hepatitis B infection, there are effective drug therapies that can control the hepatitis B virus and stop it from damaging the liver. There are also promising new drugs in the research phase that could provide a cure in the very near future. Although the risk of developing a serious liver disease or liver cancer is higher for those living with chronic hepatitis B than those who are not infected, there are still many simple things a person can do to help reduce their risk.

  • Schedule regular visits every six months (or at least every year) with a liver specialist or a health care provider who is knowledgeable about hepatitis B so they can monitor the health of your liver.
  • Talk to your health care provider about whether treatment for your chronic hepatitis B infection would be helpful in preventing serious liver disease or liver cancer.
  • Make sure that your health care provider screens you for liver cancer during your regular visits since early detection equals more treatment options and a longer life.
  • Avoid or limit alcohol and smoking since both cause a lot of stress to your liver.
  • Eat a healthy diet with lots of vegetables since fried, greasy foods are hard on your liver.


What does it mean to be a “chronic carrier”?
When someone has a chronic hepatitis B infection, their doctor may refer to them as being a “chronic carrier.” Being a “chronic carrier” means that you have a chronic hepatitis B infection, can pass the virus on to others, and you should be managed by a doctor for your infection.

Is there a cure for hepatitis B?
Most adults will recover from an acute infection on their own without the need for medication. For adults, children and infants who develop a chronic hepatitis B infection, there is currently no cure. But the good news is there are treatments that can help slow the progression of liver disease in chronically infected persons by slowing down the virus. If there is less hepatitis B virus being produced, then there is less damage being done to the liver.

With all of the new exciting research, there is great hope that a cure will be found for chronic hepatitis B in the near future. Visit our Drug Watch for a list of other promising drugs in development.


What options are there to treat my hepatitis B?
For an acute infection, there is generally no treatment other than rest and supportive measures to manage any symptoms.

For chronic hepatitis B, there are several treatments available. It is important to understand that not everyone with chronic hepatitis B needs treatment. Your doctor will help you decide if you need medication or if you can wait and monitor your condition.

There are several antiviral medications that slow down or stop the hepatitis B virus from replicating, which reduces the inflammation and damage to the liver. These antivirals are taken as a pill once a day for at least 1 year, usually longer. There are 6 U.S. FDA approved antivirals, but only three “first-line” antivirals are recommended: tenofovir disoproxil (Viread/TDF), tenofovir alafenamide (Vemlidy/TAF) and entecavir (Baraclude). First-line antivirals are recommended because they are safer and most effective. For people who do not respond to, or have access to, the first-line antiviral treatments, other options are available: telbivudine (Tyzeka, Sebivo), adefovir dipivoxil (Hepsera), and lamivudine (Epivir-HBV, Zeffix, Heptodin).

Although the FDA has approved these antivirals for chronic hepatitis B, they do not provide a complete cure. They can, however, greatly decrease the risk of developing liver damage and liver cancer. Antivirals are not meant to be stopped and started, which is why a thorough evaluation by a knowledgeable doctor is so important before beginning treatment for chronic hepatitis B.

There are also immunomodulator drugs that boost the immune system to help control the hepatitis B virus. They are given as injections over 6 months to 1 year. The most commonly prescribed include interferon alfa-2b (Intron A) and pegylated interferon (Pegasys).

You and your doctor will need to discuss the treatment options before deciding which one, if any, is best for you. For many people, these medications will decrease or stop the hepatitis B virus. This results in patients feeling better within a few months because liver damage from the virus is slowed down, or even reversed in some cases, when taken long-term.

For a complete list of FDA approved drugs and other promising drugs in development for hepatitis B, visit our Drug Watch.