የሄፓታተስ ቢ የደም ምርመራ

ለሄፓታይተስ ቢ የደም ምርመራ አለ?

በዶክተር አሊያም በጤና ክሊኒኮች የሚታዘዝ ቀላል የሆነ የሄፓታይተስ ቢ የደም ምርመራ “የሄፓታይተስ ቢ የደም ፓነል” የሚባል አለ፡፡ የደሙ ናሙና ወደ ዶክተሩ ቢሮ እንዲሄድ ይደረጋል፡፡ 

ይህንን የደም ፓናል ለማድረግ የሚረዱ 3 የተለመዱ ምርመራዎች አሉ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ሄፓታይተስ ቢ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ በመጡ ጊዜ፣ ዶክተርዎ ድጋሚ ከስድስት ወራት በኋላ መጥተው ደምዎን እንዲመረመሩ ሊነግርዎት ይችላል፡፡ እርስዎ አሁን ላይ በሄፓታይተስ ቢ እንደተያዙ ካሰቡ፣ ቫይረሱ በደምዎ ውስጥ ለመታየት 9 ሳምንታት ያስፈልጉታል፡፡

የሄፓታይተስ ቢ የደም ምርመራ ውጤትዎን መረዳት ግራ የሚያጋባ ሊሆን ይችላል፤ ስለሆነም ስለምርመራ ውጤቱ አርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል፦እርስዎ በሄፓታይተስ ቢ ተይዘዋል፣ ከሄፓታይተስ በሽታ ድነዋል ወይስ ስር በሰደደ የሄፓታይተስ ቢ በሽታ ተጠቅተዋል፡፡ 

ከዚህም በተጨማሪ የደም ምርመራዎን ውጤት በፅሁፍ መጠየቅ የትኛው ፖዘቲቭ እና የትኛው ደግሞ ኔጋቲቭ እንደሆነ ሙሉ በሙሉ ለመረዳት ያግዛል፡፡

የትኞቹ ሶስት ምርመራዎች ናቸው "የሄፓታይተስ ቢ የደም ፓነል" የሚባሉት?

የሄፓታይተስ ቢ የደም ፓነል የሚያስፈልገው አንድ የደም ናሙና ሲሆን የመጨረሻውን ምርመራ ለማድረግ ግን ሶስት ምርመራዎች ያስፈልጋሉ፦

  • HBsAg  (ሄፓታይተስ ቢ ሰርፌስ አንቲጅን)
  • HBsAb ወይም anti-HBs (ሄፓታይተስ ቢ ሰርፌስ አንቲቦዲ)
  • HBcAb ወይም anti-HBc (ሄፓታይተስ ቢ ኮር አንቲቦዲ)

የሄፓታይተስ ቢ ሰርፌስ አንቲጅን (HBsAg) ምንድን ነው? 

"ፖዘቲቭ" ወይም “ሪአክቲቭ” የHBsAg ሙከራ ውጤት ማለት ሰውየው ወይ "በመጀመሪ ደረጃ" አሊያም "ስር በሰደደ" የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ተይዟል ማለት ነው፡፡ የተያዙ ሰዎች ቫይረሱን ወደ ሌሎች በደም አማካይነት ያስተላልፋሉ፡፡


ሄፓታይተስ ቢ ሰርፌስ አንቲቦዲ (HBsAb ወይም anti-HBs) ምንድን ነው?

"ፖዘቲቭ" ወይም “ሪአክቲቭ” የ HBsAb (ወይም anti-HBs) ሙከራ ውጤት የሚያሳየው ግለሰቡ በሄፓታይተስ ቢ ክትባት ተሸሎታል አሊያም ወይም ደግሞ በመጀመሪያ ደረጃ ላይ ካለ የሄፓታይተስ ቢ ድኗል ማለት ነው፡፡  ይህ ውጤት (በኔጋቲቭ HbsAg ውጤት) ሆነ ማለት ወደፊት የሚመጣን የሄፓታይተስ ቢ ን ሰውነትህ የመከላከል አቅም አለው ማለት ነው፡፡ 


ሄፓታይተስ ቢ ኮር አንቲቦዲ (HBcAb) ምንድን ነው?

HbcAbየሚባለው አንቲቦዲ ሲሆን የቫይረሱ አካል በመሆን ለሰውነታችን ከለላ የሚሰጥ ነው፡፡ "ፖዘቲቭ" ወይም “ሪአክቲቭ” የ HBcAb (ወይም anti-HBc) ሙከራ ውጤት የሚያሳየው ከዚህ በፊት እና አሁን ላይ ስላለው መያዝ ነው፡፡ የዚህ ውጤት ማብራሪያ የሚመሰረተው በሌሎቹ ሁለት ውጤቶች ላይ ነው፡፡ በፕሮቴክቲቭ ሰርቪስ አንቲቦዲ (positive HBsAb ወይም anti-HBs) ላይ ከታየ፣ ከዚህ በፊት ግለሰቡ መያዙንና መዳኑን ያሳያል፡፡ በፀና የታመመ ግለሰብ ውስጥ ደግሞ በቫይረስ (positive HBsAg) ይታያል፡፡

 

Hepatitis B Blood Tests

Is there a blood test for hepatitis B?
There is a simple hepatitis B blood test that your doctor or health clinic can order called the “hepatitis B blood panel”. This blood sample can be taken in the doctor’s office.

There are 3 common tests that make up this blood panel. Sometimes the doctor may ask to check your blood again six months after your first visit to confirm your hepatitis B status. If you think you have been recently infected with hepatitis B, it can take up to 9 weeks before the virus will be detected in your blood.
Understanding your hepatitis B blood test results can be confusing, so you want to be sure about your diagnosis – are you infected with hepatitis B, have you recovered from a hepatitis B infection, or do you have a chronic hepatitis B infection?

In addition, it is helpful if you request a written copy of your blood tests so that you fully understand which tests are positive or negative.


What three tests make up the "hepatitis B blood panel"? 
The hepatitis B blood panel requires only one blood sample but includes three tests that are needed to make a final diagnosis:

HBsAg (hepatitis B surface antigen) 
HBsAb or anti-HBs (hepatitis B surface antibody) 
HBcAb or anti-HBc (hepatitis B core antibody)


What is the hepatitis B surface antigen (HBsAg)? 
A "positive" or “reactive” HBsAg test result means that the person is infected with the hepatitis B virus, which can be an "acute" or a "chronic" infection. Infected people can pass the virus on to others through their blood.


What is the hepatitis B surface antibody (HBsAb or anti-HBs)?
A "positive" or “reactive” HBsAb (or anti-HBs) test result indicates that a person has either successfully responded to the hepatitis B vaccine or has recovered from an acute hepatitis B infection. This result (along with a negative HbsAg result) means that you are immune to (protected from) a future hepatitis B infection.


What is the hepatitis B core antibody (HBcAb)?
The HBcAb is an antibody that is part of the virus- it does not provide protection. A "positive" or "reactive" HBcAb (or anti-HBc) test result indicates a past or present infection. The interpretation of this test result depends on the results of the other two tests. Its appearance with the protective surface antibody (positive HBsAb or anti-HBs) indicates prior infection and recovery. For chronically infected persons, it will usually appear with the virus (positive HBsAg).